Scwc News በሲዳማ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅቶች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ግቦች ዙሪያ የዉል ስምምነት ተደረገ፡፡ በሲዳማ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅቶች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ግቦች ዙሪያ የዉል ስምምነት ተደርጓል፡፡ በሲዳማ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዋና ዋና ግቦች ላይ ስምምነት ለመፍጠር በተዘጋጀዉ መድረክ የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንን ጨምሮ ሌሎች ተጠሪ የልማት ድርጅቶች ተሳትፈዋል። በዚሁ መድረክ ላይ የኮርፖሬሽናችን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በኮርፖሬሽናችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያስ ቲሮ የቀረበ ሲሆን ሌሎች ተጠሪ ተቋማትም የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በቀረበዉ ሪፖርት መሰረት በተደረገ ዉይይት ኮርፖሬሽናችን ሰፊ የልማት ስራዎችን ሲያከናዉን መቆየቱ የሚበረታታ መሆኑን እንዲሁም የልማት ድርጅቶቹ እርስ በርስ በመደጋገፍ መስራት መጀመራቸዉ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መሆኑ ተገልጿል።በመድረኩ ላይ የተገኙት የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ የልማት ድርጅቶች በየጊዜው አቅማቸውን በማሳደግና የአሰራር ሥርዓት በማሻሻል ትርፋማነትንና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራዎችን ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው እንዲሁም በተቋማቱ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ካንቹላ ካምቤ በበኩላቸው ተጠሪ ተቋማቱ የተቋቋሙበትን ዓላማ ከማሳካት ረገድ እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ እና በ2018 በጀት አመትም የበለጠ ትርፋማ እንዲሆኑ እና የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን እንዲሁም ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ሥርዓትም የሚዘረጋ መሆኑን በመግለፅ የማህበረሰብ ተኮር ሥራዎችም ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡በመድረኩ ማጠቃለያም ባለስልጣኑ ኮርፖሬሽናችንን ጨምሮ ከሌሎች ተጠሪ ተቋማት ጋር በ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ግቦች ዙሪያ የዉል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡#ሲኮስኮነሀሴ 29/2017 ዓ.ም.