የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተመረቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

‎ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተቋራጭነት የተሳተፈበት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ዛሬ መስከረም 15/2018 ዓ.ም. በክልላችን ርዕስ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና በፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
‎በሀገር አቀፍ ደረጃ በፌደራል መንግስት ተነሳሽነት የተጀመረዉ እና በሲዳማ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሲዳማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በርካታ የመንግስት አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በተደገፈ ሁኔታ በአንድ ማዕከል በዘመናዊ መልክ ማግኘት የሚያስችል ዘመናዊ ተቋም ሲሆን የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጥ ከማዘመን በተጨማሪ የዜጎችን እንግልት በእጅጉ እንደሚቀንስ ይጠበቃል። ሲዳማ መሶብ ማዕከል በአሁኑ ሰዓት በ12 ተቋማት 34 አገልግሎቶች በመስጠትም ሥራውን ጀምሯል።
‎ኮርፖሬሽናችን ለዚሁ አገልግሎት የሚውለውን የጂ+4 ህንፃ ሪኖቬዥንና ሲቪል ስራ ለመስራት ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጋር ውል በመግባት ከነሐሴ 17/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሲገነባ የቆየ ሲሆን ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር 24 ሰዓት ምሽት ጭምር በሶስት ፈረቃ በመስራት ለምረቃ አብቅቷል ።
‎መስከረም 15/2018 ዓ.ም.

Leave a Comment