የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ደስታ ሌዳሞ የጎርቼ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

ዛሬ ነሀሴ 23/2017ዓ.ም በተካሄደው የመስክ ጉብኝት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ፣ የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ስራ አስኪያጅ የተከበሩ ኢ/ር ይርጉ ታደሰ፣ የሲዳማ ሰሜናዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ብሩክ ሰለሞን ፣ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉና የዞን የመንግስት አካላት እንዲሁም የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪና ከፍተኛ የመንግስት ስራ አስፈፃሚ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ በጉብኙቱም በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት መደሰታቸዉን ገልፀዋል፡፡
ኮርፖሬሽናችን የጎርቼ ሆስፒታል ግንባታ በጥራትና በፍጥነት እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ነሀሴ 23/2017 ዓ.ም.
ጥራት ላለው ግንባታ-ሲኮስኮ

Leave a Comment