የወንዶ ገነት ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ሥራ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሀገር አቀፍ የኮሪደር ልማት አካል የሆነዉን የወንዶገነት ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እያከናወነ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽናችን ከወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ጋር በ83.3 ሚሊየን ብር የዉለታ ገንዘብ በተቋራጭነት ዉል በመግባት እያከናወነ የሚገኘዉ ይኸዉ ፕሮጀክት የላንድ ሰኬፒንግ እና የአረንጓዴ ልማት ስራ፣ የፋዉንቴን ሥራ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች ግንባታ፣ የመንገድ መብራቶች ተከላ፣ የሳይክል መንገድ እንዲሁም የልጆች መጫወቻ ቦታ ግንባታ አካቶ የያዘ ሲሆን ግንባታዉም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፕሮጀክቱን እየመሩ የሚገኙት ኢንጂነር ድሪባ ዳንሴ ገልፀዋል፡፡ በአሁን ሰዓት ኮርፖሬሽናችን የፕሮጀክቱን ግንባታ በተፋጠነ መልኩ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ይጠበቃል፡፡
ጥራት ላለው ግንባታ!
ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም.
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

Leave a Comment