የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች በፕሮጀክት የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡
የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ኮርፖሬሽኑ እየገነባቸዉ በሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመስክ በመገኘት የመስክ ምልከታና ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በመስክ ምልከታዉ አለታ ወንዶ ከተማ እና የአለታ ጩኮ ከተማ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የሩፎ ዋኤኖ አለታ ጩኮ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ግንባታ፣ የአለታ ጩኮ የቴክኒክና ሙያ ግንባታ ፕሮጀክት፣ የጎርቼ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት፣ የወንዶ ገነት ከተማ ኮሪደር ልማት እንዲሁም የወንዶ ገነት ከተማ ጂ+4 ከንቲባ ህንጻ እና ቢ+ጂ+3 የሴክተር መ/ቤቶች ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ተዟዙረዉ ተመልክተዋል፡፡ በፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም እና ከዋናዉ ቢሮ በሚፈለግ ድጋፍ ዙሪያም የፕሮጀክት ሃላፊዎች ለጎብኝዎች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉ አመራሮችና ሠራተኞች ኮርፖሬሽኑ በክልሉ በንጹህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት ግንባታ እንዲሁም በመሰረተ ልማትና በተለያዩ መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታ ተሰማርቶ እየሠራ ያለዉን መጠነ ሰፊ የግንባታ ስራ መመልከት በመቻላቸዉ እንዲሁም ባዩት የፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደትና ጥራት መደሰታቸዉን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የፕሮጀክቶች ግንባታ መሳካት የእያንዳንዱ ፈጻሚ የድጋፍ ዉጤት በመሆኑ ስራቸዉ ፍሬ አፍርቶ በማየታቸዉ መደሰታቸዉን በመግለፅ እንደነዚህ አይነት ጉብኝቶች ሠራተኛዉ ተቋሙ የሚሰራዉን ስራ ይበልጥ እንዲያዉቅ እድል ከመፍጠር በዘለለ የሠራተኛዉን ተነሳሽነት ይበልጥ የሚያሳድግ መሆኑን፣ ይህም ጉብኝት ፕሮጀክቶችን በቀጣይ ይበልጥ ለመደገፍ ከፍተኛ መነሳሳት የፈጠረ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑም አሁን ካለዉ አፈጻጸም ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስና ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ እንዲወጣ ሁሉም ፈጻሚ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡
የአለታ ጩኮ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክትን በመጎብኘት የተጀመረዉ የመስክ ምልከታም የወንዶ ገነት ቢ+ጂ+3 ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክትን በመጎብኘት ተጠናቋል፡፡